አዳም የድህረ ዘመናዊ ልብወለድ መገለጫዎችን በስፋት በመጠቀም፣ በእውነታ፣ በህይወት እና በልብወለድ መካከል ያሉ ጉዳዮችን በሂስ ለጥያቄ በማቅረብ በታሪክ እና በእውቀት መስክ አይነኬ የሆኑትን ጉዳዮች እንዲነኩ፣ የተሰቀሉ እንዲወርዱ እና እንዲጠየቁ፣ ከሌላ አቅጣጫ እንዲታዩ፣ በዚህ ውስጥም ማህበራዊ ህፀፆች ጎልተው እንዲወጡ በማድረግ ረገድ አዲስ የልብወለድ አፃፃፍ ፈር ቀዷል። በኢትዮጵያ ስነፅሁፍ ታሪክም ሌላ ደማቅ አሻራ ጥሏል ወይም አኑሯል ማለት እችላለሁ።ፀደይ ወንድሙ፡ ሐምሌ 9፡ 2003፡ በሃገር ፍቅር ቴአትር በተደረገው ውይይት የተወሰደ