... ለመውረድ ስዘጋጅ ወደኔ ዞር አለና፣"ዩ ጋት ኮንዶም?" አለኝ።"የስ" ብዬ ቦርሳዬን፣ "እዚህ ውስጥ አለኝ" በሚል ደብደብ አድርጌ አሳየሁትና ወረድኩ።እሱ በፍጥነት ወደ ቤቱ ውስጥ ሲገባ፣ እኔ ደግሞ በማይመች ጫማዬ እየተሰቃየሁና እንደ ተረሳች ውሻ ቱስ ቱስ እያልኩ እከተለዋለሁ። ከዚህ ሥራ የሚያስጠላኝ ይሄ ነው። ስለተጋዛሁ፣ የመኪና በር አይከፈትልኝም። ስለተገዛሁ፣ እጄን ተይዤ፤ ትከሻዬን ታቅፌ አልገባም። ስለተገዛሁ፣ እንደ ሰው ጎን ለጎን አልራመድም። ክፍሉ ውስጥ እንደገባን ደቂቃ እንኳን ሳያባክን ልብሱን አወላልቆ ብርድ ልብሱ ውስጥ ገባ። በብርሃን ዐየሁት። ፊቱ የእንቁራሪት ሰውነቱ ደግሞ የእንሽላሊት ይመስላል።ከዚህ ሥራ የሚያስጠላኝ ሁለተኛው ነገር ይሄ ነው። ስለተገዛሁ፣ እንቁራሪት እስማለሁ። ስለተገዛሁ፣ ለ እንሽላሊት ጭኖቼን እከፍታለሁ።ብርድ-ልብሱ ውስጥ ሆኖ የእንሽላሊት ሰውነቱን እየነካካ፣ "በምን ታፈጫለሽ... ነይና የሂሳቤን ስጪኝ እንጂ" በሚል ዐይን ያየኛል። ከዚህ ሥራ የሚያስጠላኝ ሦስተኛው ነገር ይሄ ነው። ስለተገዛሁ፣ ራሴን አሞኛል... ነገ ብናደርግ ብዬ ጥቅልል ብዬ ማደር አይፈቀድልኝም።