ይሉኝታ yelugneta.com

የራሴ ዝርዝሮችወደ የራሶ ሥፍራ

ምሳሌ

እንዳለጌታ ከበደ

ወደቋት
ዋጋ 110 ብር
facebook
ፕሮፌሰሩ ዲነግዴ ስለሚባል...ሰው ይነግሩኝ ነበር። ዲነግዴ አንድ በሬውን ሊሸጠው ገበያ ወጣ። ገበያው በየሳምንቱ ቅዳሜን እየጠበቀ የሚቆም ነው። ...በሬውን ማለዳ ይዞ ይወጣና፣ ቀኑን ሙሉ በገበያው ይውልና አመሻሽ ላይ በሬውን ይዞ ይመጣል። ይህን ድርጊቱን ደጋገመው። አንድ ቀን፣ የፕሮፌሰር ጌታቸው አባት፣ <ገዢ ጠፍቶ ነው፣ ወይስ ዋጋ አስወድደህ ነው፣ በሬህን ለመሸጥ ወጥተህ መልሰህ የምታመጣው?> አሉት። እሱም፣ <ገዢስ አላጣሁም፤ ግን በሬውን ሊገዙ ከተስማሙ በኋላ፣ ስለ አካባቢው ሁኔታ ስጠይቅ በሬዬ የሚጎዳብኝ መሰለኝ፤ በድርቆሽና ውሃ እጦት። እና በሬዬን ቀልቦ ማደር የሚችል አቅም ያለው እስኪመጣ ወደ ገበያው መመላለሴ አይቀሬ ነው> አላቸው>> ይህን ስሰማ ብድግ አልኩኝ። <ምን ሆነሃል?> አሉኝ ፕሮፌሰር።/.../
<እስከ ዛሬ ድረስ እኛ ተምረናል ዐውቀናል የምንል ልሂቃን ትልቁን ችግራችን ሃሳቦቻችንን ለማን እንደ ምንሸጥ ዐለማወቃችን ነው። ሃሳቦቻችንን ስለ ሚገዙ ሰዎች አንጠነቀቅም። ግድ የለንም። እኔ የምሸጠው ባልስትራ ተቀጥቅጦ ቆንጨራ ተደርጎ መጥቶ እኔን፣ ወይም ወገኔን ካረደ በጉዳዩ ላይ የእኔ እጅ የለበትም ማለት እችላለሁ?> አልኳቸው።
እሳቸውም፣ <ዐየህ! መማር ማለት እንደ እዚህ ነው። አንዳንዴ ዘቅዝቀህ፣ ወይም ገልብጠህ ነገሮችን በተለየ መንገድ ለመረዳት መሞከር። ና ግንባርህን ልሳምህ!> አሉኝ፣ ጥንታዊ ብራና የመሰለ ፊታቸውን በፈገግታ እየገላለጡ፣ ከዊልቸራቸው ነቅነቅ ብለውም፣ እጃቸውን ዘረጉልኝ። እጃቸው ከሌላው ሰውነታቸው ቀደም ብሎ የነበረ የተፈጠረ ይመስለኛል፤ በአጼ ዘርዐያዕቆብ ዘመን አንዱ ደቀ እስጢፋ ለእሳቸው ተናዞላቸው የሔደ...
/ከመጽሐፉ የተወሰደ/

የመመዝግቢያ ቅጽ

ስም
የአባት ስም
የአያት ስም
የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል
የሚስጢር ቃል እንደገና ፃፍ
ለመግዛት ለመሸጥ ለሁለቱም

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

የመላኪያ አስራሻዎን ያስገቡ

ሁሉም መልዕክቶች በEMS (ኢኤምኤስ) ስለሚላኩ አድራሳዎን ስም እስከ አያት ፡ ስልክ ቁጥር (መድረሱን ደውለው የሚያረጋግጡበት ስለሆነ) ፡ የቤት ቁጥር ፡ የአካባቢ ስም(የጎጥ ስም) ፡ የቀበሌ ስም ፡ ወረዳ ፡ ክልል በማለት ያስገቡ።


X