<<... አቤል ራሱን ማመን አቅቶት የመታወቂያ ወረቀቱን ከኪሱ አውጥቶ የመለያ ቁጥሩን ተመለከተ። ያ ቁጥር ሰሌዳው ላይ የለም። ማለፉም ሆነ መውደቁ የግድ ሰሌዳው ላይ መውጣት አለበት። እና ፣ የአቤል ከዚህ ከሁለቱ ውጭ መሆን ምን ሊሆን ይችላልን?...>>ደራሲ ሲሳይ ንጉሡ በ1977 ዓ.ም. ይህንን መፅሐፍ ሲያሳትም ዩኒቨርስቲ የአራተኛ ዓመት ተማሪ ነበር። ከዚያ በኋላ ግርዶሽ፣ ትንሳኤ፣ የቅናት ዛር እና ረቂቅ አሻራ የተሰኙትን ረዣዥም ልቦለዶች አስነብቦናል።ሰመመን ከአሁን ቀደም ስድስት ጊዜ በተደጋጋሚ የታተመ ሲሆን ተወዳጅነትን በማትረፉና ተፈላጊነቱ እየጨመረ በመምጣቱ እነሆ ለሰባተኛ ጊዜ ታትሞ ቀርቧልመልካም ንባብ!