የተረጋጋ ስሜትና የአእምሮ ሰላም እንዲኖርዎት ይሻሉ?የሚያሳድጉት ልጅ አለዎች? ስለ ነገው ስብዕናውስ ያስባሉ?የትዳሬ ነገር አንዱ ትልቅ ጉዳዬ ነው የሚሉ ባለትዳር ነዎች?በስርዎ ያሉት ሠራተኞች ለመምራት የልብዎ ያልደረሰልዎች ኃላፊ ነዎት?በማኀበራዊ ሕይወትዎ ያዝ የሚያደርግዎት ውስጣዊ ችግር የለብዎትም?እስካሁን ያላስተዋሉት አንድ የሚያስፈልግዎ ቁልፍ ነገር አለ፤ በደንብ በሚረዱት አቀራረብ እያስገነዘበ የሚመራዎ ይህ ስሜትና አእምሮ መጽሐፍ ነው።በተለይ ደግሞ አላግባብ የሚናደዱ፣ የሚጨነቁና ጨለምተኛ በሆነ የስሜት ባሕር ውስጥ ገብተው እየሰመጡ ከሆነ አሁን የነፍስ አድን ጀልባ ያስፈልግዎቻል።ጀልባው ይህ ሣይንሳዊ የሆነ የሥነ-ልቦና መጽሐፍ ነው።የቀደመውን የመጽሐፉን ዕትም ካነበቡ በኋላ በስልክ ከተሰጡ የአንባቢያን አስተያየቶች መካከል፡በሥነ ልቦና፡ እንደዚህፍንትው አድርጎ የሚያብራራ መጽሐፍ አልገጠመኝም። ፈጣሪ ፀጋውን ያብዛልህ።አንድ መጽሐፍ እንደዚህ ይለውጠኛል ብዬ አስቤም አላውቅም ነበር።አማርኛ ቋንቋ በደንብ ለማይችሉ ኢትዮጵያዊያን በሌሎችም ቋንቋ እንዲተረጎም ብታደርገው።