ከፍቅር... ከቀፎውን አትንኩት... ከሌዋታን... ከሃምሳለቃ ገብሩ.... ከሰዶም ፍፃሜ እና ከሚመጣው ሰንበት... ደራሲ᎐ ᎐ ᎐......ቋንቋና መዋቅሩ /the plot/ በጣም ጥሩ ናቸው። የፓለቲካ ጭብጡ ስላቅ ነው። የዘመናችንን ውጥንቅጡ የወጣና ግራ የሚያጋባ ሁናቴን ድህና አድርጎ ያንጸባርቃል።ደራሲ ሣህለሥላሴ ብርሃነ ማርያም"ሙኢና ቁኢ ተጥንት ጀምሮ ፈጣሪ ለአለም ሁሉ በሚተርፍ ፍቅር የባረካቸው ህዝቦች ነበሩ። እስተ ቅርብ ጊዜ ድረስም በቋንቋ ተለያይተን.. በዘር ተጣልተን አናውቅም። እኔ ሙኢው በነሱ ሰፈር ሳልፍ አንድ ቁኢ የተመለከተኝ እንደሆን ከተቀመጠበት ደጃፍ ተነስቶ ወደ እኔ ይሮጣል። ማንነቴን ሳያውቀው... ዘሬም ሳያስጨንቀው ሰው መሆኔን ብቻ አስቦ ይጠመጠምብኛልየኔን ሙኢኛ ባይችልም የሱን ቁኢኛ ባልናገርም በራሱ ቋንቋ "ምድን ወተ ንላም ላሰው" በማለት "ምን ገጠመህ አንተ ሰው" ሲለኝ እኔም በቋንቋዬ "ምንተ ንአ ራብክ ያው ሰው" እያልኩ እጅ እነሳዋለሁ"᎐ ᎐ ᎐"ወቸው ጉድ!!" ይላሉ።"የምን ጉድ ነው እማማ ኩንዳሬ?" ስንላቸው"ህዝቡን እርስ በርስ አጣልተው ያጨራርሱታል ብለን የምንፈራው እነዚህን ሰዎች አይደለምን?""ነው""መንግስትስ ህዝቡን ከነዚህ ክፉ ሰዎች ሊጠብቅ አይገባም ትላላችሁ?""ይገባል እንጂ እማማ ኩንዳሬ""ታዲያ ህዝቡን ከነዚህ ሰዎች ክፋት መጠበቅ ትቶ ጭራሹን ያጠፉናል ብለን ለምንሰጋቸው ለነዚህ አውሬዎች ጠባቂ መቅጠሩ ምን ብናስቀይመው ነው?"ከመፅሐፉ የተወሰደ