አቶ ሀብታሙ አለባቸው የፓለቲካ ጉዳዮች ተመራማሪና የሰመረላቸው የሥነ ጽሑፍ ሰው ናቸው። አውሮራ(2006)፡ የቄሳር እንባ(2007)፡ እና የሱፍ አበባ(2008) የተሰኙ መጽሐፎቻቸው በብዙ ሺህ ቅጂዎች ታትመው ተሸጠውላቸዋል። ይህ 4ኛው መጽሐፋቸው ኮስታራ ነው። ፍጽም የማይደፈሩ ርዕሰ ጉዳዮችን አንስቷል። በዋናነት ዛሬ የደረስንበትን ፓለቲካዊ ምስቅልቅል ከሥር መሠረቱ ለመፈተሽ ይሞክራል።