ነቃማይ ምጡቅ ሰማይነቃማይን ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ድብቅ በሆነው ሚስጥራዊ ታሪኩ ባውቀውም ፤ በዚህ መፅሐፍ ላይ ግን የተለየ ሚስጥር ጫረብኝ። መሳጭና ልብ አንጠልጣይ ታሪክ አካቷል፤ ፍፁም የውስጣችንን መሻት የሚረዳ የፍቅር ታሪኮችም አሉት። አንድ ጊዜ ከጀመሩት ሳይጨርሱት ቀና አይሉም።መምህር መሪጌታ ዘውዱ መሰሉነቃማይ ወደ ኋላ በትዝታ ፈረስ ሸምጥጦ፤ በትንቢት ደግሞ ወደ ፊት እየጋለበ ወደ ላይ ይዞን ያቀናል።ነቃማይ ከቶ በአንድ ታሪክ ችክ ብሎ አናገኘውም፤ ታሪክን፣ ድብቅ ሚስጥራትን፣ ሐይማኖታዊና ፓለቲካዊ ሁነቶችን እያመሳጠረ ከቦታ ቦታ እንደ ዓባይ ሙላት ይዞን ይነጉዳል።ሌላው ደግሞ ነቃማይ የነፍስ አድን መፅሐፍ ነው ብል አንባቢ አይቀየመኝም ፤ (G.dragon) ስለሚለው ልብስና ስለአፋልጉኝ ማስታወቂያ እስከ ምክንያቱ ሚስጥሩን ያብራራል።ደራሲና ገጣሚ ያረጋል እጁጉ