መጠየቅ የሚፈቀድና የሚገባ መሆኑን ብቻ ሳይሆን በመጠየቅ ዓለማችንን መፍጠር እንደምንችል ያሳየኝ መጽሐፍ ነው።ወ/ሮ ሶሎሜ ታደሰይህ ድርሰት ጣምራ ተቃራኒ ፆታ ባህርያትን ፈጥሮ በገሃዱ ዓለም የምናውቃቸው እስኪመስለን ድርስ ገጠመኞቻቸውን ያስዳስሰናል። ከሐኪም ቤት፤ ምግብ ቤት፤ ማረሚያ ቤት፤ መኖርያ ቤት፤ መቃብርቤት እያለ ከህይወት እስከ ሞት ባለው ጽንፍ ያለውን ሂደት ያሥቃኘናል። በበርካታ ግጥሞቹና በግጥም መድበሉ የምናውቀው ገጣሚ ሐኪምነቱ መምህርነቱና በኋላ የደረበው የፍልስፍና ዕውቀቱ ከሰብዓዊነቱ ጋር ተዳምረው ደራሲ ዳዊት ወንድማገኝ መፈጠር መወለድና መኖርን ባንድ ወገን በሌላ ገጽ ደግሞ የአለመኖርን ፍልስፍና በመበርበር ያስደምመናል። በዚህ ድርሰት ውስጥ መተሳሰብ፤ ፍቅር፤ ጥላቻ፤ ቅናት፤ የጊዜ አጠቃቀም ሥርዓት፤ ሥልጣን፤ ይሉኝታ፤ ጉራ፤ መኖር፤ መሞት የመሳሰሉት ከመኖር እስከ አለመኖር ባለው ቋት ውስጥ ያላቸውን መስተጋብር በሚገባና ቋንቋ ስላቀረበልን በአዲሱ ካባው ዳዊትን "ዕደግ ተመንደግ እያልኩ ለተደራስያኑ መልካም የንባብ ጊዜ እመኛለሁ!"ዶ/ር መስፍን አርአያየአእምሮ ሐኪምና መምህር"አለመኖር"በአንድ መፅሐፍ ውስጥ ሃሣብን በዚህ መልኩ ማንሳት ይቻላል እንዴ? መፅሐፉን ሳነበው መጀመርያ ወደ አዕምሮዬ የመጣ ጥያቄ ነው። በመፅሐፉ ውስጥ ያልተነሳ ሃሳብ የለም ማለት ይቻላል፤ እኔን የመሰጠኝ ግን የሃሳቦቹ በግርድፉ መነሳት ሳይሆን ሃሳቦቹ የታዩበት አውታርና ጥልቀት ነው። ልማዳዊ ከሆነው ዕይታ ውጪ ነገሮችን ማየትም ሆነ መመርመር ውጉዝ በሆነበት በዚህ ማህበረሰብ፤ "አለመኖር" ነገሮችን ከመሰረታቸው በመነቅነቅ "ለካ እንዲህም አለ!" ወደሚል መደመም መክተት ብቻ ሳይሆን የዕይታ መነፅራችንን እንደ አዲስ ወደ መምረጥና ማስተካከል ትገፋለች ቁምነገሩም እሱ ይመስለኛል።ዳንኤል ለማለማንበብ የማያስቸግር ትረካ የታሪኩ አስተዳደግ ፈጣን በአስተማሪነቱ እንደ ግለሰብ ማሕበረሰብ አገርና መንግስት ሁልጊዜ ከእኛ ውጭ ያለውን ማየት መገምገምና አውቅልሃለሁ ማለት ብቻ ሳይሆን ራስን ወደ ውስጥ መመልከት በጣም አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ ከፍተኛ መልእክትን ያዘለ የፍልስፍና ሥራ ብል ማጋነን እንደማይሆን አንባቢውም አንብቦ እንደሚያረጋግጥ አልጠራጠርም።ዶ/ር አብነት ታፈሰየውስጥ ደዌ እና የነርቭ በሽታዎች ሐኪምና መምህር