ይህ መጽሐፍ ልቦለድ ነው ቢሉኝ እንዴት አምናለሁ? የተኖረን ሕይወት እየተረኩ <<ልቦለድ> ብሎ ነገር አለ እንዴ?የአሥመራዊያንና የአጋሜን ፍጥጫ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራን አያዎ (paradox)፣ የመሪዎቻችንና የመሪዎቻቸውን ዝምድናና ቁርሾ፣ የባድመን አሰቃቂ እልቂትና ረብ የለሽ ጦርነት ደራሲው በግሩም ሁኔታ ዘግቦታል። ...እውነቱን ለመናገር ደራሲው የሚጽፈውን የሚያውቅ ሰው ነው።...ደፋር አትበሉኝና ይህንን መጽሐፍ በጭብጥና ይዘቱ ስመዝነው ከኦሮማይ በኋላ የተፈጠረ ድንቅ የጥበብ ሥራ ነው ብዬ አፌን ሞልቼ እናገራለሁ።