ይደመቆ በተባለ ተራራ በሰኔ ወር 1932 የተነሳ ፎቶግራፍከግራ ወደ ቀኝ መሃል ዝቅ ብለው የተቀመጡት ማሞ ሥዩም (በኋላ ደጃዝማች)፤ ከፍ ያለ ወንበር ላይ የተቀመጡት ግራዝማች ተሾመ ሽንቁጥ (በኋላ ደጃዝማች)፤ አጠገባቸው ወንበር ላይ የተቀመጡት ልጅ አበበ ሽንቁጥ (በኋላ ደጃዝማች)፤ አጠገባቸው ልጅ ተድላ መኮንን (በኋላ ሜ/ጀነራል)፤ ከሳቸው ላይ የቆመው ሕጻን ዓለማየሁ አበበ (በኋላ አምባሳደር)። ከግራዝማች ተሾመ ሽንቁጥ ጀርባ ወጣት ጫንያለው ተሾመ (በኋላ አምባሳደር)። ፊት ለፊት መሬት ላይ ከተቀመጡት መሃል ምልኬ ጩፋ (በኋላ ግራዝማች) በቀኝ ከሳቸው አጠገብ አጋፋሪ ሽሽጉ። ከጀርባ ከቆሙት መካከል ይታገሱ ጠጋው መታፈሪያ አዲሴ ካሣ የሚባሉ አሉበት።