ይሉኝታ yelugneta.com

የራሴ ዝርዝሮችወደ የራሶ ሥፍራ

ኢምንት ዕድል

አብይ በላይነህ

ወደቋት
ዋጋ 85 ብር
facebook
ስሟ ከ40 ጊዜ በላይ በመጽሃፍ ቅዱስ የተፃፈላት፤ ወንዟ በኦሪት ዘፍጥረት ገነትን እንደሚያጠጣ የተመሰከረላት፤ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉነቱን አይለቅም የተባለላት፤ እግዚአብሔር ከገዛ ወገኖቹ አስበልጦ የተመለከታት የዚህች ሀገር ሕዝቦች በሰማይና በምድር ፈጣሪ ላይ ማጉረምረምን ያዙ። "እውን እግዜሩ በመንበሩ አለን?" አሉ።

...የምታውቀው ታሪክና የሰማችው ተደበላለቀባት። በዚህ ሁኔታ የትኛው የሀገራችን ታሪክ ነው እውነት? በምስራቅ ነው ያሉት ነገር ምናልባት መነሻው ምዕራብ ሊሆን እንደሚችል አሰበች። ሟች ተብሎ ለዘመናት ሲዘከር የነበረው ሰው ምናልባት ገዳይ ሊሆን እንደሚችል ገባት። ሰው ዘመን ላይ ሲራመድ ሁሌም የራሱን ስም ከፍ አድርጎ ሰቅሎ ማለፍ ዋንኛው አላማው እንደሆነ ብታውቅም ታሪክን ገልብጦ ማስቀመጥ ግን ምን ያክል ጥፋት እንደሆነ እያሰበች በሀሳብ ነጎደች። ሁሉም የራሱን አስተሳሰብ ብቻ ትክክል ነው ብሎ በሚያስቀምጥበት ዓለም ላይ ታሪክን ያለማስረጃ እውነተኛ ነው ብሎ መቀበል የዋህነት እንደሆነ ተረዳች።

...እሳት የሆነው መፅሀፍ ኢየሱስ መጥቶ በአባይ ውሀ እስከሚታጠብ ድረስ ውሀ የሆነውን መፅሀፍ አጥቶ ቆየ። ይህ የውሀ ምልክት ያለበት መፅሀፍ ከጀልባይቱ ስሪት የተረፈውን ኢየሱስ የታጠበበት ወዙን ለመጀመሪያ ጊዜ ከጠጣው ከአቶ ዮቶርን ይጀምራል። የቀኝ እጁ ግማደ መስቀል እግዜሩ በመረጠው በመስቀልኛ ቦታ ሲያርፍ ይህ የውሀ ጠብታ ያለበት ትንሽዬ መፅሀፍ በዮቶርን የልጅ ልጅ ልጅ ላይ አረፈ።

"...እንደዚህ አይነት ስራዎች ብዙ ጊዜ ሰርቻለሁ። ሁሉም አብሮኝ ወደ መቃብር የሚወርድ ሚስጢር ነው ያሉትን ነገር ስቃዪ እየጨመረ ሲሄድ ለመዳን ሳይሆን ቶሎ ሞተው ከስቃዩ መገላገል ስለሚፈልጉ ብቻ መናገራቸው የማይቀር ነው። አንቺ ደግሞ እንደማይሽ ቆንጆ ሴት ነሽ። መቼም ይሄ ሰውነትሽ እንዲበጣጠስ የምትፈልጊ አይመስለኝም፤ ስለዚህ ወደዚህ ሁሉ ጣጣ ከመግባታችን በፊት በኋላ የምትነግሪኝን ሚስጢር ለምን አሁን አትነግሪኝም። ልጅሽ የት ነው ያለው?" ብሎ በትኩረት ተመለከታት።
... ከመጽሐፉ የተወሰደ

የመመዝግቢያ ቅጽ

ስም
የአባት ስም
የአያት ስም
የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል
የሚስጢር ቃል እንደገና ፃፍ
ለመግዛት ለመሸጥ ለሁለቱም

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

የመላኪያ አስራሻዎን ያስገቡ

ሁሉም መልዕክቶች በEMS (ኢኤምኤስ) ስለሚላኩ አድራሳዎን ስም እስከ አያት ፡ ስልክ ቁጥር (መድረሱን ደውለው የሚያረጋግጡበት ስለሆነ) ፡ የቤት ቁጥር ፡ የአካባቢ ስም(የጎጥ ስም) ፡ የቀበሌ ስም ፡ ወረዳ ፡ ክልል በማለት ያስገቡ።


X