ይሉኝታ yelugneta.com

የራሴ ዝርዝሮችወደ የራሶ ሥፍራ

ኤቶዮጵ

ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ

ወደቋት
ዋጋ 130 ብር
facebook
1፤ መሠረታቸው በተቀደሱ ተራሮች ነው፤
2፤ ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል።
3፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ በአንቺ የተከበረ ነገር ይባላል።
4፤ የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፤እነሆ፥ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ በዚያ ተወለዱ።
5፤ ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።
6፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።
7፤ በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።
(መ.ቅዱስ ፨፨፨ መዝሙረ ዳዊት፤ ምዕራፍ-87)

..."እነዚያ በምድር ላይ ሃያል የሚሆኑት አይሁዶችን ለአማኝ ሙስሊሞች በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ሆነው በእርግጥ ታገኛቸዋለህ። እነዚያ፤ "እኛ ክርስቲያኖች ነን!" የሚሉት ደግና ለአማኝ ሙስሊሞች በወዳጅነት በእርግጥ ይበልጥ የቀረቧቸው ሆነው ታገኛቸዋለህ ይህም የሆነው ከእርሱ(ከእውነተኛ ክርስቲያኖች) መሃል(ጥሩ) ቀሳውስትና ዓለምን የናቁ መነኮሳት በመኖራቸው እነርሱም የማይኮሩ(ትሁቶች) በመሆናቸው ነው።"
(ቅ.ቁርዓን ፨፨፨ የማዕድ ምዕራፍ፤ ቁ.82)

ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ፥ እንደ ሩሲያዊው ደራሲ አንቷን ቼኮቭ በሙያው ሀኪም ነው። ሆኖም ለስነጽሁፍ ባለው ፍቅር ጊዜውን አጣቦ እየፃፈ ሁለት መፃፍትን በእንግሊዝኛና በአማርኛ ከዚህ ቀድሞ አስነብቦናል። አሁን ደግሞ በዚህ በአስገራሚ ልብወለድ መጥቷል።

ይህ መጽሀፍ የማይነኩና የማይደፈሩ ጥልቅ መንፈሳዊ ጉዳይዎችን ያዘለ ነው። አእምሮው በሳይንስ ከተቀረጸ ምሁር ከሳይንስ ተጻራሪ የሆነ ይዘት ማውጠንጠኑ ብዙም ያልተለመደ ነገር ነው።
የኢትዮጵን የልጅነት ስም ኢትኤልን ለዋናው ባለታሪክ ሰጥቶ እና ሌሎች ከእሱ ጋር የሚጓዙ ጽዮን፣ አብርሃም፣ መርየም፣ ቶላ፣ ናዖድ፣ ቢታንያ፣ ዘይኔና ዮሴፍ የተሰኙ ባህርያትን ፈጥሮ ታሪኩን በህክምና ትምህርት በተሰማሩ ተማሪዎች መሀል አሰናስሎ ጀምሮ እንደ ፕ/ር እሴና ዶ/ር ሳሙኤል ባሉ ምሁሮች አጅቦ እስከ አስገራሚዎቹ ባህታዊ፣ ወልዮችና አባ-ገዳዎች ድረስ አዋዝቶ ያዳርሰዋል።
ደራሲው ከሚያነሳቸው ርእሶች ውስጥ ዛሬ የኢትዮጵያን ኅብረተሰብ የተበተበው የጥንቆላ አስከፊነት አንዱን ስፍራ ይዟል። በተጨማሪም ገናናውን የኢትዮጵያ ታሪክና የ"ቶ" ጥበብን ይዳስሳል። ከእዚህ ሁሉ በላይ በጠቅላላው የኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች እና ክርስትያኖች ጥንታዊ ግንኙነትና ወዳጅነት፥ እንዲሁም በእስልምና እና ክርስትና ሀይማኖቶች መሀል የአሉትን ተመሳሳይነት፥ አንድነት እና ኅብረት አጉልቶ ያንጸባርቃል።
ታሪኩም ምስጢራዊ እና መንፈሳዊ ሆኖ፥ እያጓጓ እና እየተሽቆለቆለ ይፋስሳል። ቃላቱና አ/ነገሮቹም በቦታቸው ገብተው እርስበርሳቸው ተዋህደዋል። ይህን መጽሀፍ ሁሉም ሰው ቢያነበው የፈንጠዝያ(inspiration)ን እና የአእምሮውን አድማስ ያሰፋል ብዬ አስባለሁ። (ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ)

የመመዝግቢያ ቅጽ

ስም
የአባት ስም
የአያት ስም
የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል
የሚስጢር ቃል እንደገና ፃፍ
ለመግዛት ለመሸጥ ለሁለቱም

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

የመላኪያ አስራሻዎን ያስገቡ

ሁሉም መልዕክቶች በEMS (ኢኤምኤስ) ስለሚላኩ አድራሳዎን ስም እስከ አያት ፡ ስልክ ቁጥር (መድረሱን ደውለው የሚያረጋግጡበት ስለሆነ) ፡ የቤት ቁጥር ፡ የአካባቢ ስም(የጎጥ ስም) ፡ የቀበሌ ስም ፡ ወረዳ ፡ ክልል በማለት ያስገቡ።


X