መንበር ከጠመንጃ አፈሙዝ ብቻ በሚፈልቅበት ሀገራችን አመራር ጥበብ አመራር እውቀት ተደርጎ አይታሰብም። ደራሲ ዲረዓዝ ይህን ዘመን ያስቆጠረ ዕሳቤ በመለወጥ አመራር ሳይንስ፣ መሪነት ጥበብ እንደሆነ በግል በቡድን፣ በማህበረሰብ ከዚያም ከፍ ብሎ እንደሃገር ራሳችንን ልናስተዳድርበት ስለሚገባው ጉዳይ ጠጣሩን የንድፈ-ሃሳብ ቋጥኝ አላልተው መሬት በማስነካት የመሪነትን ሚስጥር እንካችሁ ይሉናል።ዶ/ር ምህረት ደበበየ20ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን ወደ ስልጣኔና ዕድገት ለማሸጋገር ምሁራኖቿ ጃፓን እንደምን ሠለጠነች፣ መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር ምንገጽታ ይኑረው በማለት ዳር ዳሩን ይሽከረከሩበት የነበረውን ቁልፍ ጉዳይ ከሸፈነው አይናፋርነት በማላቀቅ እርካብና መንበር በሚል ርዕስ የዘመናችንን የስጋት ምንጭ ብቻ ሳይሆን መፍትሄያዊ አማራጩንም በመዘርዘር ለዛ ባለው ቋንቋ ለአንባቢ በማቅረብ ደራሲ ዲራዓዝ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ናቸው ማለት ይቻላል።ዶ/ር አብዱልረዛቅ ሙህየዲን