አዳም ረታ የ ምሕሌት፣ ግራጫ ቃጭሎች፣ አለንጋና ምስር፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር እና ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ ደራሲ ነው። አሁን ደግሞ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ የተሰኘውን የትረካዎች ስብስብ ይዞላችሁ ቀርቧል።አዳም በዚህ መጽሐፉ ወደራሳነውና ወደምናስታውሰው፤ ወደአከበርነውና ወደናቅነው፤ ወደሸሸነውና ወደምንቀርበው፤ ወደፈራነውና ወደደፈርነው ዓለም ይወስደናል።