<<እቴጌ ጣይቱ እጅግ ጠንካራና የሚያደርጉትን ነገር በሚገባ የሚያውቁ፤ የአስተዳደር ጥበብን የተካኑ ቢሆኑም በሴትነታቸው አነስተኛ የሆነ ድክመት አላጣቸውም። ለእኝህ ሴት ያለኝ አክብሮት ታላቅ ነው።>>ተፈሪ መኮንን (ንጉሠ-ነገሥት ኃይለሥላሴ)<<እቴጌ ጣይቱ ብጡል የፓለቲካ ስብዕና ማካቬሊያዊ የፓለቲካ መሠሪነት የታከለበት ነበር። ቀስ በቀስ የባለቤታቸውን በትረ-ሥልጣን በስውርም ሆነ በግልፅ ለመቆጣጠር ድብቅ፣ ግን እምቅ ፍላጉት ነበራቸው።>>ኒኮላ ደ አሚቶ<<ጣይቱና ምኒሊክ በዘመቻቸው በአሜሪካ የፕቴዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር በእጩነት ቢቀርቡ ኖሮ መላውን ግዛት ለማስተባበርና አንድ ለማድረግ የሚያስችል ትልቅ አቅም ያላቸው በመሆኑ ጣይቱ ማሸነፋቸው አይቀርም ነበር።>>ክሪስ ፑዮቲር<<እኛ ጥንታዊ ሕዝቦች ነን። ሐገራችንም ጥንታዊት ናት። በእርግጥ አሁን እኛ አነስተኛና አቅመ-ቢስ ሆነን ልንታይ እንችላለን። ታላቅ ሕዝብና የገናና ሐገር ባለቤት ለመሆን ግን አውሮፓውያን አያስፈልጉንም። ንጉሡ አፄ ምኒልክ አማካሪዎች የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ከራሳችን ሕዝብ ውስጥ አማካሪዎችን መርጠን መሰየም እንችላለን>>እቴጌ ጣይቱ ብጡል(ፈረንሳዩ ዲፕሎማት ሊዮንስ ላ ጋርዴ፣ እቴጌይቱን ጠቅሶ ካሰፈረው)<<እቴጌ ጣይቱ ከሀገራቸው በቀር ለሌላው አለም ብዙም ትኩረት የማይሰጡና ሀገራቸውንም ከተቀረው አለም ጋር ማወዳደር ያለመፈለግ ቁትጠኝነት እንደሚታይባቸው እንድገነዘብ ስላደረጉኝ ዝም ማለትን መረጥኩ።>>አልፍሬድ ኢልግ<<ይህች ለዘመናት ከአለም ተገልላ የቆየች ክርስቲያን ሐገር ብዙም ያልተዳሰሰች በመሆኗ የልዑካን ቡድኑ ትኩረት ሰጥቶ በሐገሪቱ የሚገኙ የአትክልትና የአዝዕርት ዝርያዎችን እንዲያጠና፣ ዘራቸውን ይዞ እንዲመጣ፣ በዚያች ሐገር በብዛት ይገኛል የሚባለውን የሜዳ አህያ ዝርያ ውሃ ጥምን የመቋቋም አቅም እንዳለው ስለሚነገር ሲመለሱ የሜዳ አህያ ግልገሎችም ይዘው እንዲመጡ ይሁን።>>የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቴዲ ሩዝቬልትወደ አቢሲኒያ የሚሄደውን ቡድን መሪ አግኝተው ባነጋገሩበት ወቅት