...በመሃሉ በፍርሀትና የአድናቆት በሚመስል ቃና ዶ/ር ማግሊና፥"ሲሳይ!" አለችኝ። "አቤት" ብዬ ፊቴን ወደ እርሷ ፊት ለፊት ወደ ታች እጇን ዘርግታ ፥ "Oh my God. I think that tree is moving!"(ኦ አምላኬ! ያ ዛፍ ይንቀሳቀሳል) አለች።"Ya every tree moves with the wind"(አዎን ማንኛውም ዛፍ በነፋስ ይንቀሳቀሳል) አልኳት ለማቃለል ብዬ። እንደ እውነቱ ከሆነ እኔም በከፍተኛ ፍርሀት ውስጥ ነበርኩ።"No, no I mean it is moving not swinging" (አይደለም አይደለም! መወዛወዝ ሳይሆን ይንቀሳቀሳል ነው ያልኩህ) አለች ኮስተር ብላ።"What?!"(ምን?!) አልኩ..."እንዲያው ያለአቅሜ ለዘመናት ተቆልፎ የኖረ ምሥጢር ነካክቼ ልሰቃይ" አልኩና በምሬት፥ "አይ ፕሮፌሰር ሃሮልድ! እግዜር ይይለዎት። በሞኝ ክንድ የዘንዶ ጉድጓድ ይለኩበታል የተባለው ተረት በእኔ ደረሰ" አልኩ። ስቃዩን በሙሉ ዋጥ አድርጌ ራሴን እጅግ እየተራገምኩ እንዳይደረስ የለም <ግዝት በር> ላይ ደረስን። ከአንድ ዛፍ ሥር ቁጭ አልኩና የውስጥ እግሬን ሳየው የተጠበሰ ሥጋ መስሏል፤ ዐልፎ ዐልፎ ደግሞ ውኃ ቋጥሯል።..."በፍለጋው በመድከምም ሆነ በመሰላቸት በዚያው መቅረትም አልተፈቀደልህም። ወደ ቅዱሱ ቦታ ለመመለስ በዘገየህ ቁጥር የኋለኛው ዘመንህ እንደምንጣፍ ወደ አንተ እየተጠቀለለ ይቀርባል።"......በወረትና በጉጉት የጀመርኩት ምሥጢር ማነፍነፍ እንዴት ያለ ዋጋ እንዳስከፈለኝ አስቤ <ሲያንሰኝ ነው!> አልኩ። በምን ምክንያት እንዴት ባለ ሰበብ ወደዚህ መንከራተት እንደገባሁ ሳስብ ሕይዎት በዕጣ ፈንታና በአስደናቂ ገጠመኞች የተሞላች መሆኗ ታሰበኝ።... ከመጽሐፉ የተወሰደ