የቼክ ሪፐብሊኩ ተወላጅ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ አዶልፍ ፓርለሳክ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገሮችን የጎበኙ ሲሆን፣ እ᎐ኤ᎐አ በ1935 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በመምጫት ከንጉሠ ነገሥቱ ፊት ቀርበው የኢትዮጵያን መኰንንነት ማዕረግ ከተሾሙ በኋላ የሰሜኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ለነበሩት ራስ ካሣ ኃይሉ የጦር አማካሪ በመሆን አገልግለዋል። በዚሁ ወቅት በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጎን ሆነው ታግለዋል። መጽሐፉ፣ ሃበሽስካ ኦዴሳ (Habesska Odyssea) - የሃበሻ ጀብዱ፣ የዚያን የገበሬ ጦር ጀግንነት ለመዘከር የጻፉት ነው።