"አይበገሬው ሰው እንዴት ከጉዞው እንደተሰናከለ ወይም ነገሮችን እንዴት በተሻለ መልኩ መፈጸም ይችል እንደነበር በሩቅ ሆኖ አስተያየቱን የሚሰጠውም፣ ከዳር ተቀምጦ ትችቱን የሚሰነዝረውም በጉዳዩ ውስጥ ቦታ የላቸውም። በተግባር የፍልሚያው ሜዳ ውስጥ ገብቶ በጀግንነት ሲዋደቅ ሁለመናው በአቧራ፣ በደምና በላብ ለጨቀየው ለራሱ ለባለ ጉዳዩ ነው እውቅናው የሚገባው። በጥረት ውስጥ ስህተትና ጉድለት አያታጣምና፣ ስኬትን ሊጎናጸፍ በልበ ሙሉነት ሲጣጣር ስህተት የፈጸመው፤ ከጉዞው ደግሞ የተሰናከለው፤ ያም ሆኖ ግን አላማውን ለማሳከት ከመጣር የማይቦዝነውና መቼም ቢሆን ጥረቱን የማይገታው፤ ጥልቅ ስሜቶችንና ታላላቅ መስዋዕትነቶችን ጠንቅቆ በመረዳት ላመነበት ነገር ራሱን የሚሰዋው፤ ከቀናው የላቀ ስኬትን ድል በወጉ ለማጣጣም፣ ካልሆነለት ደግሞ ድልንም ሆነ ሽንፈትን አይተው ከማያውቁት ድንጉጥና ፈሪ ነፍሶች ተርታ አንድም ቀን ራሱን ላለማሰለፍ በጽናት እየታገለ እስከ ፍጻሜው የሚዋደቀው የአይበገሬው ጀግና ነው - ክብርና ሞገሱ።"ቴዎዶር ሩዝቬልት(የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት)"አምባር" ወይስ "ብዕር"?መንገደኛ ልጅነትየበደኖው ዘማችከ"በር" እስከ "ወንበር"ወደ ዎልስትሪት"ሮያል ክራውን" በግፍ ከዙፋን የወረደ ንጉስውሃን ሽቅብ ማውጣት"ምከረን ብለውኝ...""ዘመነ - ዘመን"የሰቆጣው ብረትአክሰስ ሪል ስቴት - ትልቅ ህልም፣ ትልቅ ቀውስ"ያቺ ጋዜጣ..."ማዕበሉ እስኪያልፍዳግም ወደ ፍልሚያው ሜዳ"ኮሎኔሉ..."መላ ይዞ፣ መላ ማጣት...የፍጻሜው ጦርነት 128 ቀናት- በማዕከላዊ እስር ቤት