አሮሌ የሃያ ዘጠኛ ዓመት ወጣት ነው። መልከ መልካም፣ መለሎ። ትምህርቱን የጨረሰባትን የሀምቡርግ ከተማ ለቆ በጦርነት ወደምትታመሰው ሀገሩ የተመለሰው ይህንኑ አሁን ሽጉጥ ይዞ የሚዝትበትን ሰው አምኖ ነበር። ምዕራብ ጀርመን ያሉ ወዳጆቹ መክረውት ነበር እንዳይመለስ። አስጠንቅቀውት ነበር ሊደርስበት የሚችለውን ችግር እያስረዱ። ማስጠንቀቂያቸውን ግን ችላ አለው። ስራና የመኖሪያ ቤት ካገኘ፤ መኪና ማስገባት ከቻለ፤ የልጅነት ፍቅረኛውን አግብቶ ከኖረበት ማህበረሰብ ጋር መቀላቀልን እንደትልቅ ፀጋ ነበር የቆጠረው። በእድሜ የገፉ አሳዳጊ አባቱን በህይወት ማግኘት ችሎአል። ጂብሪል ቃል የገባለትን የመኖሪያ ቤትና የስራ ጉዳይ ጨረሰለት። ያጣው ቢኖር የልጅነት ፍቅረኛውን ብቻ ነበር። ሀወኒ ትባላለች። አገር ምድሩን አስሶ የገባችበትን ማወቅ አልቻለም። ቢሆንም ኑሮው መልካች መሆን ጀመሮ ነበር። የዛሬው ዱብእዳ ግን እንግዳ ሆነበት። በጀርመን ሀገር ቆይታው ትምህርቱን ተግቶ ከመከታተል አልፎ የጎላ የፓለቲካ ተሳትፎ አልነበረውም። ፓለቲከኞች ግን ከልቡ ነበር የሚንቃቸው። አሁን ግን ጂብሪል <<የየትኛው ድርጅት ቃፊር ነህ?>> ሲል አፋጦ ይዞታል።ከመጽሐፉ የተወደሰ