ከአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት በኋላ ለአምስት ዓመታት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ እና የኢህአዴግ ምክርቤት አባል በመሆን ከጽድቁም ሆነ ሃጢአቱ ተቋዳሽ ሁኛለሁ። የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በማእከላዊ ኮሚቴ፣ በኢህአዴግ ምክርቤት፣ በጉባኤዎች እና ሌሎች ወሳኝ መድረኮች ቤት ዘግተው ብዙ ነገር ብለዋል። ነገር ግን ህዝቡ በዝርዝር እንዲያውቀው አልተደረግም። በዚህ መጽሐፍ ከውስጥ የነበረውን ሁኔታ "እንደወረደ" ቀርቧል።ስለሆነም መጽሐፉ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ከጊዜ ወደ ጊዜ ለምን እና እንዴት ተዳከመ? ድርጅቱ ከውድቀት መዳን ለምን ተሳነው? የድርጅቱ ቁንጮ መሪዎች ስለ ድክመታቸው እና የድርጅቱ የቁልቁለት ጉዞ ምን ይሉ ነበር? በመካከላቸው የነበረውን ግንኙነት እና የስልጣን ሽኩቻ ምን ይመስላል? በአመራሩ የሚስተዋል ሌብነት እና ኪራይ ሰብሳቢነት ለመፋለም የነበራቸው ቁርጠኝነት ምን ድረስ ነበር? የትኛው ብሄራዊ ድርጅት ምን አይነት ተሳትፎ ነበረው? ማን የለውጥ ሃይል ማን እንቅፋት ነበር? በድርጅቱ ለምን የበሰለ መሪ እና አመራር ጠፋ? የሚሉ እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ዳሷል?