በመጀመሪያ በእንግሊዘኛ በታተመበት ጊዜ ዕውቅ ምሁራን የሰጡት አስተያየት፤ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ እጦት አሁን በሚያስደስት ሁኔታ ተሟልቷል። እንዲህ ያለን መጽሐፍ መጻፍ በብዙ መንገድ አዳጋች ቢሆንም፤ ደራሲው ግዴታውን በሚገባ ተወጥቶታል። የነገሥታትና የጦረኞችን የፓለቲካ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ኤኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ክንዋኔዎችን ያትታል። ያገር ውስጥ ክስተቶች ከውጭ እያደገ ከሚመጣው ግፊት ጋር ተዛምደዋል። የደራሲው አስተያየቶች ውል ያልሳቱና ብርሃን የሚፈነጥቁ ናቸው። በውስጡ ያሉት አያሌ ፎቶግራፎች ለመጽሐፉ ተጨማሪ ዋጋ ሰጥተውታል።ፕሮፌሰር ክርስቶፈር ካላፕሃምላንካስተር ዩኒቨርሲቲ(እንግሊዝ)ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ አንስቶ እስከ 1966 አብዮት ላለው የኢትዮጵያ ታሪክ ከዚህ የተሻለ መጽሐፍ አለ ብሎ ማሰብ ያዳግታል። መጽሐፉ ብዙ መረጃዎችን ይዞ አዳዲስ ግኝቶችንም ይፈነጥቃል። በኢትዮጵያዊ ደራሲ የተጻፈ የመጀመሪያው የቅርብ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ በመሆኑም ልዩ ግምት ይሰጠዋል።ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስትየኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም(አዲስ አበባ)ስለ ሁለተኛው የእንግሊዝኛ እትም የተሰጠ አስተያየትሁለተኛው እትም ውስጥ የተካተተው አዲስ ምዕራፍ (ምዕራፍ 6) የዘመናዊቱ ኢትዮጵያን ታሪክ ለመረዳት ለሚሻ አንባቢ ሁሉ መጽሐፉ ያለውን ዋጋ ይበልጥ ያጎላዋል። በ44 ገጾች ተጨምቆ የቀረበው የአብዮቱ ዘመን ታሪክ በ1970ዎቹ የተፃፉትን አያሌ መጻሕፍት፥ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎችን ጥናትና የደራሲውንም የየግል ተሞክሮ አጣቅሶ በጥንቃቄ የተቀመመ በመሆኑ፤ ራሱን የቻለ ዋጋ ያለው ነው። እንደ መጀመሪያው እትም ሁሉ፤ ትረካው ብርቅ በሆኑ ፎቶግራፎች የተቀነባበረ ነው። ባጭሩ ተሻሽሎና ዳብሮ የቀረበ ትልቅ ዋጋ ያለው መጽሐፍ ነው።