ይሉኝታ yelugneta.com

የራሴ ዝርዝሮችወደ የራሶ ሥፍራ

የኢትዮጵያ ፍልስፍና የዘርዓያዕቆብና የወልደ ሕይወት ሐተታዎች ትንታኔ (ከነሐተታቸው)

ብሩህ ዓለምነህ

ወደቋት
ዋጋ 80 ብር
facebook
ዘርዓያዕቆብና ወልደ ህይወት በ17ኛው ክ/ዘ ያገኙት ማህበረሰብ በቁሳዊ ሐብቱ የደኧዬ፣ በዓለማዊ ህይወቱ እጅግ የተጎሳቆለ ነው።

ካህናቱ መንፈሳዊ ህይወትና ዓለማዊ ህይወት ተጫራቾች አለመሆናቸውን በማስተማር ህዝቡ ከወደቀበት የጉስቁልና ህይወት እንዲያንሰራራ ማድረግ ይችሉ ነበር። ሆኖም ግን ካህናቱ ይሄንን ነገር ማድረግ ባለመቻላቸው የእነዚህን ሃይማሮታዊ ልሂቃን ሸክም ለመሸከም የመጡት ዘርዓያዕቆብና ወልደ ህይወት ናቸው።

በመሆኑም የዘርዓያዕቆብና የወልደ ህይወት አዲሱና መሰረታዊ ፍልስፍና "የሰው ልጅ መንፈሳዊ ከፍታን የሚያመጣው የተደላደለ ቁሳዊ መሰረት ሲኖረው ነው፤" የሚል ነው።

Monastic life had been an existential problem for millennia for Ethiopia.

"ለቅዱስ ያሬድ ይህ ዓለም በመላ ልክ እንደ ትልቅ ማህሌት(ሲንፎኒ) ነው፤ ፍጥረታት ሁሉ በአንድነት በዜማ የሚያመሰግኑበት ሲንፎኒ።" ይሄም ማለት ቅዱስ ያሬድ ተፈጥሮን የሚገነዘበው በቀለሙ፣ በልስላሴው አሊያም በቅርፁ ሳይሆን በድምጹ ነው - ፈጣሪውን በሚያመሰግንበት ዜማው ነው። ለዚህም ነው "ደምፀ አገሪሁ ለዝናም" (የዝናብ እግሩ ተሰማ) ያለው - ዜማን ከዝናብ ድምፅ ፈልቅቆ ሊያወጣ!!! የ6ኛው ክ/ዘ ባህል እንደዚህም ዓይነት አስደናቂ ሰው ፈጥሯል።

ማህበረሰቡ የቆመበት ልማድና የአፈታሪክ መሰረት ላይ የመጀመሪያውን አመጽ ያካሄዱት ዘርዓያዕቆብና ወልደ ህይወት ናቸው። ይሄም የፈላስፎቹ ፕሮጀክት ለማህበረሰቡ አዲስ መሰረት ፍለጋ ነው።

በቤተ ክርስትያን ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የዳበረው ይሄ የተቀባይነት መንፈስና የሚጠይቅን ተማሪ የመኮርኮሙና ስም ለጥፎ የማጥቃቱ ልማድ በሀገሪቱ የፓለቲካ ሥርዓት ውስጥም ሰርጎ ገብቷል።

ዘርዓያዕቆብ አክሱም ላይ ወንበር ዘርግቶ ሲያስተምር "ማጥመቅ" የሚለውን ሃይማኖታዊውን የትምህርት ዓላማ "ወገንተኛ ሳይሆኑ መመርመርና መጠየቅ" በሚለው ተካው፣ "ማነብነብ" የሚለውን የማስተማሪያ ዘዴ ደግሞ "መወያየትና መከራከር" በሚለው ዘዴ ለወጠው። ይሄ ነው የዘርዓያዕቆብ የትምህርት አብዮት!!!

የአፄ ቴዎድሮስን የዘመናዊነት ፕሮጀክት ሊሸከም የሚችለው ነባሩ ሃይማኖታዊ ትምህርት ሳይሆን የዘርዓያዕቆብና የወልደ ሕይወት የስነ ሰብዕ ትምህርት ብቻ ነው። የእነዚህ ፈላስፎች የባህልና የእምነት ፍተሻ የአብርሆት ዘመንን በማምጣት በኋላ ላይ አፄ ቴዎድሮስ ላይ ለሚጀመረው የዘመናዊነት ፕሮጀክት አስቀድሞ የባህል መደላደል የመፍጠር አቅም ነበረው።

አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመናዊ ትምህርት አንድ ዋነኛ ተልዕኮ እንዲኖረው ይፈልጉ ነበር። ይሄውም ከትውሪታዊው ትምህርት ጋር እንዲጣመር።

የመመዝግቢያ ቅጽ

ስም
የአባት ስም
የአያት ስም
የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል
የሚስጢር ቃል እንደገና ፃፍ
ለመግዛት ለመሸጥ ለሁለቱም

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

የመላኪያ አስራሻዎን ያስገቡ

ሁሉም መልዕክቶች በEMS (ኢኤምኤስ) ስለሚላኩ አድራሳዎን ስም እስከ አያት ፡ ስልክ ቁጥር (መድረሱን ደውለው የሚያረጋግጡበት ስለሆነ) ፡ የቤት ቁጥር ፡ የአካባቢ ስም(የጎጥ ስም) ፡ የቀበሌ ስም ፡ ወረዳ ፡ ክልል በማለት ያስገቡ።


X