"ደራሲው" -የበዓሉ ግርማ አራተኛ ልብወለድ መጽሐፍ። ሕይወት፣ ድርሰትና ደራሲ ሲወሳሰቡ በከያኒ ስሜት ውስጥ ጭንቀትና ሐሴት ሽንፈትና ድል ይፈራረቃሉ....ሲራክ - የመጽሐፉ መሪ ገጸ-ጋህርይ - ብዕሩ ነጥፎ ውበት ስትከዳው፣ ባዶው ነጭ ወረቀት ባዶ ሆኖ መልሶ ሲያፈጥበት ይጨነቃል፣ ሰላም ያጣል፣ ከራሱ-- ከሰው-- ከፈጠራቸው ገፀ-ባህርያትና ከድርሰት ጋር።ታዲያ ሲራክ ሰላም እንዳጣ ይቀር ይሆን? ወይስ ከእውነታ ጥልቀት ውስጥ ውበት ፈንጥቃ ስትወጣ ሲያይ፣ ከራሱ ዓለም ከመያው ጋር ይታረቃል?ኪነት ነው --- ድርሰት።