...ሰብለወንጌልም የዛ ህልውና ትግል ቀዳሚ ተሳታፊ ነበረች፤ ለአማራ ህልውና መትረፍም ባለውለታ ሴት ናት። በደስታ ቀን ካበቡት ሰዎች ይልቅ በመከራ ቀን ስልምልም ያሉት ሰዎች የበለጠ ዋጋ አላቸው። ሆኖም ሰብለወንጌል በመከራ ጊዜ እንደ ጸሀይ ያበራች ሀያል የአማራ ሴት ናት። ሰብለወንጌል የአማራ ጸሀይ ነበረች። የአምላክ ጸሀይ ስትጨልም ያበራች የአማራ ወይዘሮ ጸሀይ።ጥያቄዎች ቀጠሉ... አንድ ተሳታፊ እንዲህ አለ። "...እኔ መጠየቅ የምፈልገው የአማራ ህዝብ ምን እንዳደረጋችሁ ነው... ምን አድርገናችሁ ነው ግን? እውነት ይሔ ሆደ ሰፊ ህዝብ እናንተን ያስከፋ ሁኖ ነው?... እንዴው ምን አድርገን ነው... እናንተ ዙራችሁ የማታዩትን ድንበር በጠበቅን? ስለ ሀገር ደህንነት እያልን እየቆሰለን በቻልን.. የእሞትን ዝም ባልን? እውነት በጣም ያሳዝናል... በጣም! አሁን ዝምታው ተሰብሯል፤ የሚሰራብን ደባ ቁልጭ እና ፍንትው ብሎ እየታየን ነው። ህወሃት ይህችን ሀገር እንደሚያፈራርሳት ግልፅ ነው። እንደ ኢትዮጵያዊ መሬቱን አብረን አርሰን እንብላ ስንል... እንደ አማራነታችን ማንነታችንም መሬታችንንም እናስመልሳለን።"