ይሉኝታ yelugneta.com

የራሴ ዝርዝሮችወደ የራሶ ሥፍራ

ፍቅር እስከ መቃብር

ሀዲስ ዓለማየሁ

ወደቋት
ዋጋ 118 ብር
facebook
ደራሲ ክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ሰለሞን በ1902 ዓ᎐ም᎐ ጎጃም ደብረማርቆስ አውራጃ እንዶዳም ኪዳነምሕረት ተወለዱ።

አያታቸው የዜማ መምሕር ስለነበሩ እዚያው በተወለዱበት አገር በስድስት አመታቸው ፊደል መቁጠር ጀምረው አስራአምስት አመት እስኪሆናቸው ድረስ የዜማ ትምህርት ሲከታተሉ ቆይተው ከዚያም ደብረ ኤሊያስ፣ ደብረወርቅና ዲማ በሚባሉ አድባራት እየተዘዋወሩ የቅኔ ትምህርት ተምረው አጠናቀዋል።

በ1918 ዓ᎐ም᎐ አዲስ አበባ መጥተው መጀመሪያ በስዊድን ሚሲዮን ቀጥሎም በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ከተማሩ በኋላ መጀመሪያ በተማሩበት በስዊድን ሚሲዮን ቀጥሎም ጎጃም ዳንግላ ደብረማርቆስ በአስተማሪነት አገልግለዋል።

በ1928 ዓ᎐ም᎐ ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ስትወር ማስተማሩን ትተው በዚያህ ዘመን የጎጃም እንደራሴ ከነበሩት ልዑል ራስ እምሩ ኃይለስላሴ ስር ሆነው ትግራይ ሽሬ ግንባር ዘምተዋል።

ከዚያም 1929 ዓ᎐ም᎐ በታህሳስ መጨረሻ ላይ ጌራ ላይ ከተደረገው ትልቅ ጦርነት በኋላ ጅማንና ከፋን በሚያዋስነው ጎጀብ ወንዝ ላይ ተከበው ተይዘው ወዲያውኑ ወደ ጣሊያን አገር ተግዘው በ1936 ዓ᎐ም᎐ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጣሊያንን ድል አድርገው በያዙት በእንግሊዝና በካናዳ ወታደሮች እስኪፈቱ ድረስ ፓንዛና ሊፓሪ በሚባሉ ደሴቶች በኋላም ከላይቤሪያ ውስጥ ሎንግቦኮ በሚባል ተራራማ ገጠር ከሰባት ዓመት በላይ ታስረዋል።

በ1936 ዓ᎐ም᎐ ከጣሊያን ተመልሰው በጋዜጣና ማስታወቂያ መስሪያ ቤት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ ተቀማጭነታቸው እንግሊዝ ሀገር ሆኖ የእንግሊዝና የሆላንድ አምባሳደር ከዚያም መልስ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፤ የህግ መወሰኛ እና የብሄራዊ ሸንጎ አባል ሆነው በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በሃላፊነት አገልግለዋል።

ደራሲ ክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ በድርሰት ዓለም የተሰማሩት ገና ወጣት ተማሪ ሳሉ ነበር። የመጀመሪያ የፈጠራ ድርሰታቸው ያበሻና የወደኋላ ጋብቻ የተሰኘ ተውኔት ሲሆን በወቅቱ የተመልካችን ልብ የሳበ ነበር።

ከግዞት ከተመለሱ በኋላ የትምህርትና የተማሪ ቤት ትርጉም ተረት ተረት፤ ፍቅር እስከ መቃብር፤ ወንጀለኛው ዳኛ፤ የልምዣትና ትዝታ የተባሉ ድርሰቶቻቸውን ለአንባቢያን አቅርበዋል።

የመመዝግቢያ ቅጽ

ስም
የአባት ስም
የአያት ስም
የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል
የሚስጢር ቃል እንደገና ፃፍ
ለመግዛት ለመሸጥ ለሁለቱም

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

ወደ የራሶ ሥፍራ ለመግባት

የመጠቀሚያ ስም
የመጠቀሚያ የሚስጢር ቃል

የመላኪያ አስራሻዎን ያስገቡ

ሁሉም መልዕክቶች በEMS (ኢኤምኤስ) ስለሚላኩ አድራሳዎን ስም እስከ አያት ፡ ስልክ ቁጥር (መድረሱን ደውለው የሚያረጋግጡበት ስለሆነ) ፡ የቤት ቁጥር ፡ የአካባቢ ስም(የጎጥ ስም) ፡ የቀበሌ ስም ፡ ወረዳ ፡ ክልል በማለት ያስገቡ።


X